የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ካቢኔ ባደረገው አመደበኛ ስብሰባው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በመወያየት ውሳኔዎችን አሳልፏል።
የክልሉ ካቢኔ የከተማ ኢንቨስትመንትን ውጤታማ ለማድረግ በዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶችን ወደ ስራ ለማስገባት እና መሬት ወስደው ወደሥራ ባልገቡ ባለሃብቶች እርምጃ አወሳሰድ ዙሪያ ተወያይተዋል።
ካቢኔው በክልሉ በከተማ ኢንቨስትመንት ለመሠማራት መሬት ወስደው በውሉ መሠረት በወቅቱ ያላለሙ ባለሃብቶች መኖራቸውን አጽንኦት ሰጥቶ ተወያይቷል።
በዚህም ቀደም ሲል ለባለሃብቶች ተሰጥቶ የነበረ እና በወቅቱ ያልለማ 50 ሺህ ካሬ ሜትር መሬት ከባለሃብቶች ተነጥቆ ወደ መሬት ባንክ እንዲገባ እና ለአልሚ ባለሃብቶች እንዲተላለፍ ውሳኔ አሳልፏል።
በተጨማሪም የከተማ ኢንቨስትመንት ቦታ የወሰዱ ከ80 በላይ ባለሃብቶች በአጭር ጊዜ ወደ ልማት እንዲገቡ ያሳሰበው ካቢኔው፣ የቅርብ ክትትል ተደርጎ በወቅቱ ወደልማት የማይገቡ ከሆነ አስፈላጊው እርምጃ እንደሚወሰድ ውሳኔ አሳልፏል።
The Benishangul Gumuz Regional Government Cabinet held an informal meeting and passed decisions on various agendas. The regional cabinet discussed the issue of putting investors engaged in the sector to work to make urban investment effective and taking action against investors who have not taken land and have not started work. The cabinet discussed and emphasized that there are investors who have taken land for urban investment in the region and have not developed it in time according to the contract. Accordingly, it has decided that 50 thousand square meters of land that was previously given to investors and was not developed at that time should be taken from the investors and transferred to the land bank and transferred to developing investors. In addition, the cabinet, which urged more than 80 investors who have taken urban investment sites to start development in a short time, decided that necessary action will be taken if they do not start development in time.
عقد مجلس وزراء حكومة منطقة بني شنقول غوموز اجتماعا غير رسمي وأقر قرارات بشأن أجندات مختلفة. ناقش مجلس الوزراء الإقليمي قضية وضع المستثمرين المشاركين في القطاع للعمل على جعل الاستثمار الحضري فعالا واتخاذ إجراءات ضد المستثمرين الذين لم يأخذوا الأرض ولم يبدؤوا العمل. ناقش مجلس الوزراء وأكد أن هناك مستثمرين أخذوا أراضٍ للاستثمار الحضري في المنطقة ولم يطوروها في الوقت المناسب وفقًا للعقد. وبناءً على ذلك، قرر أن يتم أخذ 50 ألف متر مربع من الأراضي التي تم منحها سابقًا للمستثمرين ولم يتم تطويرها في ذلك الوقت من المستثمرين ونقلها إلى بنك الأراضي ونقلها إلى المستثمرين الناميين. بالإضافة إلى ذلك، قرر مجلس الوزراء، الذي حث أكثر من 80 مستثمرًا أخذوا مواقع الاستثمار الحضري على البدء في التطوير في وقت قصير، اتخاذ الإجراءات اللازمة إذا لم يبدأوا التطوير في الوقت المناسب.
© Waza Technology Institute. All Rights Reserved. Design by Waza Technology Institute