በህዝቡ የተደመረ አቅምና የተጠናከረ ተሳትፎ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ገለጹ።
አቶ አሻድሊ ሀሰን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ሀገራችን ኢትዮጵያ ለፅንፈኛ የፖለቲካ አስተሳሰብና ለፅንፈኛ ፖለቲከኞች የማትመች ሆና እየተገነባች ያለች፣ የህዝብን ፍትሃዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት መነሻዋም መድረሻዋም በማድረግ ብልፅግናዋን ለማረጋገጥ እየተጋች የምትገኝ ታሪካዊት ሀገር ነች ብለዋል።
እንደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በዚህ የብልፅግና አስተሳሰብ በተቃኘ ሀገራዊ ጉዞ ውስጥ የበኩላችንን ተደማሪ ውጤት ለማከል ህዝባችንን አስተባብረን ኃላፊነታችንን እየተወጣን እንገኛለን ሲሉም ገልጸዋል።
"በአንድ እጅ አጨብጭቦ በአንድፈረስ ስቦ" እንደሚባለው ስኬታማነታችን የሚረጋገጠው በህዝባችን የተደመረ አቅምና የተጠናከረ ተሳትፎ እንጅ በተናጠል ባለመሆኑ ይህንኑ አጠናክረን እንቀጥላለንም ነው ያሉት።
ፅንፍ እና ፅንፈኝነት ፈፅሞ ተቀባይነት የላቸውም ያሉት አቶ አሻድሊ፣ ህዝብን ከህዝብ በመነጠል የሚገኝ የፖለቲካ ትርፍ ባለመኖሩ እንዲህ ዓይነቱ ዘመን ያለፈበት የሤራ ፖለቲካ ፈፅሞ ቦታ እንደሌለውም በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
The efforts to ensure prosperity through the combined power and strong participation of the people will continue, said President Ato Ashadli Hassan. In a message posted on his social media page, Ato Ashadli Hassan said, “Our country, Ethiopia, is a historical country that is being built in a way that is not conducive to radical political thinking and radical politicians, and that is striving to ensure its prosperity by making the people’s fair participation and benefit its starting point and destination.” He also stated that we, as Benishangul Gumuz region, are fulfilling our responsibility by coordinating our people to contribute to this national journey towards prosperity. "As the saying goes, 'Clap your hands together and ride your horse together', our success will be determined by the combined power and strong participation of our people, not by individual efforts, and we will continue to strengthen this," he said. Stating that extremism and radicalism are completely unacceptable, Ato Ashadli wrote on his social media page that there is no place for such outdated conspiracy politics as there is no political gain from isolating the people from the people.
وقال الرئيس أتو أشادلي حسن إن الجهود الرامية إلى ضمان الرخاء من خلال القوة المشتركة والمشاركة القوية للشعب ستستمر. وقال أتو أشادلي حسن في رسالة نشرها على صفحته على وسائل التواصل الاجتماعي: "إن بلدنا إثيوبيا بلد تاريخي يتم بناؤه بطريقة لا تفضي إلى التفكير السياسي الراديكالي والسياسيين الراديكاليين، ويسعى جاهداً لضمان ازدهاره من خلال جعل المشاركة العادلة للشعب والاستفادة منه نقطة انطلاقه ووجهته". كما ذكر أننا، كمنطقة بني شنقول غوموز، نفي بمسؤوليتنا من خلال تنسيق شعبنا للمساهمة في هذه الرحلة الوطنية نحو الرخاء. وقال: "كما يقول المثل، "صفقوا بأيديكم معًا واركبوا حصانكم معًا"، فإن نجاحنا سيحدده القوة المشتركة والمشاركة القوية لشعبنا، وليس بالجهود الفردية، وسنواصل تعزيز ذلك". وأكد أتو أشادلي على صفحته على مواقع التواصل الاجتماعي أن التطرف والراديكالية أمر غير مقبول على الإطلاق، وأنه لا مكان لمثل هذه السياسات التآمرية العتيقة لأنه لا توجد فائدة سياسية من عزل الناس عن الناس.
© Waza Technology Institute. All Rights Reserved. Design by Waza Technology Institute